HEALTH

ስለቶንሲላይቲስ (Tonsillitis) ምን ያህል ያውቃሉ?

በጉሮሮአችን ውስጥ በግራና በቀኝ ሁለት የቶንሲል ዕጢዎች ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ዕጢዎች በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ መጠቃት ቶንሲላይቲስ የተሰኘ በሽታ ያመጣል፡፡ በጣም የታወቀው ቶንሲል የሚያመጣው ባክቴሪያ ስትሬፕቶከክስ ፓዮዲኒስ ይባለል፡፡
ሁለት የቶንሲል ዕጢዎች በአፋችን የሚገቡ ማንኛውንም ጀርሞችን በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅማቸው ተጠቅመው ስለሚዋጉ በባክቴሪያዎች እና ቫይረሶች በተደጋጋሚ ጥቃት ይደርስባቸዋል።
ይህ በሽታ በቀላሉ መከላከልና ከተያዝንም መዳን የሚቻል ሲሆን በተደጋጋሚ በዚህ በሽታ መጠቃት ግን ለኩላሊት፣ ለልብ፣ለቆዳ ማበጥ፣ለቁርጥማትና መሰል በሽታዎች ከማጋለጡም በላይ ለሞት ይዳርጋል፡፡
በባክቴሪያ የሚተላለፈው ቶንሲላይቲስ ዕድሜያቸው ከ5-15 ያሉ ህፃናትን የሚያጠቃ ሲሆን በቫይረስ የሚተላለፈው ቶንሲላይቲስ ግን በተለየ ሁኔታ ወጣቶችን ያጠቃል፡፡
☑️ በቶንሲል ስለመያዛችን የሚጠቁሙን ምልክቶች
1. ሁለቱ የቶንሲል ዕጢዎች ቀልተው ያብጣሉ፡፡ ቢጫ ወይም ነጣ ያለ ምልዕክት ይታይባቸዋል፡፡
2. እስከ 39.4 ዲግሪ ሴንግሬድ የሚደረስ ከፍተኛ ትኩሳት
3. ጉሮሮ በጣም ከመቁሰሉ የተነሳ ምግብ ለመዋጥ መቸገር (ምግብ ሲመገቡ የጉሮሮ ሕመም መሰማት)
4. አንገታችን ስር ያሉ ሊምፍኖድስ የተሰኙ ዕጢዎች ማበጥ ወይም መጠኑ መጨመር
5. ከፍተኛ ድካም (ለሕፃናት)
6. መጥፎ አተነፋፈስ፣ምላስ መድረቅ፣የታፈነ ድምፅ
7. የአንገት መገተር፣ብርድ ብርድ ማለት፣የሆድ ሕመም (ወጣት ልጀች)
8. እንዲሁም ጀርባን፣እጅንና እግርን ማሳከክ ናቸው፡፡
☑️ የቶንሲል ሕክምና
1. ቀለል ያለ ሕመም ከሆነ ጨው በተቀላቀለበት ሞቅ ያለ ውሃና በሎሚ ጭማቂ የጉሮሮ ወስጠኛውን ክፍል ማፅዳት
2. ጉሮሮአቸውን ለማጠብ ለሚቸገሩ ሕፃናት ጀርም የሚያጠፋ ኃይለኛ ያልሆነ መድኃኒት በጉሮሮአቸው ውስጥ መርጨት
3. በጅንጅብል የተፈላ ሻይ (ቀሽር ሻይ መጠጣት)
4. ቶንሲሎቹንም በቀን አንድ ጊዜ ጀርም የሚገድል መድኃኒት መቀባት
5. የጉሮሮው ቁስል በታወቀበት (በተሰማበት) ቀን የሆድ ማለስለሻ መድኃኒት መውሰድ
6. ለሁለት ወይም ለሦስት ቀናት ያህል ቀጠን ያሉ ምግቦችን መመገብ ( እጥሚት፣ሾርባ እና ገንፎ የመሳሰሉት)
7. ብዙ ውሃና የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት የሞቀ ቢሆን የተሻለ ነው
☑️ የቶንሲል በሽታን እንዴት እንከላከል?
1. ልጅዎ መፀዳጃ ቤት ደርሶ እንደተመለሰ እና ምግብ ከመመገቡ በፊት ሁል ጊዜ እጁን በውሃና በሳሙና በአግባቡ እንዲታጠብ ያድርጉ፡፡
2. ልጅዎ በጋራ እንዳይመገብ፣ መጠጫ ብርጭቆዎች፣ የፕላስቲክ ጠርሙሶችና ሌሎች የመመገቢያ ዕቃዎችን ከሌሎች ጋር እንዳይጋራ ያደርጉ፡፡
3. ቶንሲላይቲስ ሕመም እንደያዘው ከተረጋገጠ የጥርስ ብሩሹን ይቀይሩለት፡፡
4. ልጅዎ ከታመመ ቤት ውስጥ እንዲቆይ ያድርጉት (በፍፁም ወደ ት/ቤት ወይም ጨዋታ ቦታ እንዲሄድ አያድርጉ)፡፡
5. ልጅዎ ወደ ት/ቤት መቼ እንደሚመለስ ሐኪሙን ይጠይቁ፡፡
6. ልጅዎ በሚስልበትና በሚያስነጥስበት ጊዜ በሶፍት ወይም በክንዱ እንዲሸፍን ይንገሩት፡፡
7. ልጅዎ በሚስልበትና በሚያስነጥስበት ጊዜ እጁን በውሃና በሳሙና እንዲታጠብ ያስተምሩት።
biniesh
I am and Ethiopian Blogger and computer Enthusiast.
http://www.binishare.com/wp

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

29 + = 31