HEALTH

የትርፍ አንጀት በሽታ (Appendicitis)

 

የትርፍ አንጀት በሽታ (Appendicitis)

 

በትርፍ አንጀት ማበጥ እና መቅላት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ የትልቁ አንጀት ቅጥያ ሲሆን 3 ½ የሚረዝም ቁመት አለው፡፡ ስለ ትርፍ አንጀት እርግጠኛ ሆነን መናገር የሚቻለው ነገር ቢኖር ትርፍ አንጀታችን ተወግዶ መኖር መቻላችን ነው፡፡

የትርፍ አንጀት ድንገተኛ ህክምና የሚያስፈልገው ሲሆን ትርፍ አንጀትን ለማስወገድ ቀላል የሆነ ቀዶ ጥገና ይሰራል/ይደረጋል፡፡ ካልታከምነው እና በቀዶ ጥገና ካልተወገደ ያበጠው ትርፍ አንጀት ይቀደዳል ወይም ይበሳል ከዚያም ኢንፌክሺየስ(ጐጂ) ነገሮችን ወደ ከርሳችን(ሆድ) ይለቀቃል የዚህም ውጤት በህክምና ቋንቋ ፐሪቶኖሲስ የሚባለው እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ፐሪቶኖሲስ ከባድ የሆነ የከርስ(ሆድ) ሽፋን መቅላትና ማበጥ ሲሆን በጣም በፍጥነት በከፍተኛ ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶች ካልታከምነው ገዳይ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ መግል የቀላቀለ ከሌሎች የሰውነት ክፍል የተነጠለ ካበጠው የትርፍ አንጀት ውጪ ይከሰታል በዚህ ጊዜ ኢንፌክሽን ወደ ከርስ እንዳይዛመት ስካር ቲሹ() ትርፍ አንጀትን ከሌሎች የከርስ ክፍል ለይቶ ይሸፍናታል፡፡ ያበጠ ትርፍ አንጀት አስቸኳይ ህክምና የማስፈለግ ሁኔታው ዝቅተኛ ነው ነገር ግን ከቀዶ ጥገና ውጪ መለየት አይቻልም በዚህ ምክንያት ነው ሁሉም የትርፍ አንጀት ህመሞች በድንገተኛ/ኢመርጀንሲ() እንዲታከሙ የሚደረገውና ቀዶ ጥገና የሚደረግላቸው፡፡

በአሜሪካ ከ 15 ሰዎች ውስጥ አንዱ የትርፍ አንጀት ተጠቂ ናቸው፡፡ ትርፍ አንጀት በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያለን ሰው የሚያጠቃ ሲሆን ከ 2 ዓመት በታች ባሉ ህፃናት ላይ የመታየት እድሉ ዝቅተኛ ሲሆን እድሜያቸው ከ 10- 30 የሚሆናቸው ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ ይታያል፡፡

✔ የትርፍ አንጀት መነሻ

ትርፍ አንጀታችን በዓይነ ምድር፣ በባዕድ ነገር ሲዘጋ እና በካንሰር የትርፍ አንጀት በሽታ ይከሰታል፡፡ የትርፍ አንጀት መዘጋት በኢንፌክሽን ሊከሰት ይችላል ምክንያቱም ትርፍ አንጀታችን በሰውነታችን ለሚከሰት ማንኛውም ኢንፌክሽን ምላሽ ስለሚያብጥ ነው፡፡
የትርፍ አንጀት ምልክቶች
የትርፍ አንጀት በሽታ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታል፦
• በእምብርት ወይም የላይኛው የሆድ ክፍል የሚጋጥም ከባድ ህመም፡፡ ይህ ህመም ወደታችኛው ቀኝ የሆድ ክፍል ስንሄድ ህመሙ በጣም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህ የመጀመሪያው የትርፍ አንጀት ምልክት ነው፡፡
• የምግብ ፍላጐት መቀነስ
• ማቅለሽለሽ እና/ወይም ማስመለስ የሆድ ህመም ከጀመረን በኋላ
• የከርስ/ሆድ ማበጥ
• ከ 37-39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ ትኩሳት/ሙቀት
• ማግሳት አለመቻል

ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ምልክቶች ደግሞ እነሆ፦
• በላይኛው ወይም ታችኛው የሆድ ክፍል የሚያጋጥም ከፍተኛ/ከባድ ህመም
• የጀርባ እና ፊንጢጣ ህመም
• ሽንት ስንሸና ከፍተኛ ህመም መኖር
• ከሆድ ህመም በፊት ማስመለስ
• ከፍተኛ ቁርጠት
• የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ካየን በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ተገቢ ነው ምክንያቱም እያንዳንዱ የሠዓት ሽርፍራፊዎች ይህን በሽታ ለማከም በጣም ወሳኝ ነው፡፡ መብላት፣ መጠጣት፣ የህመም ማስታገሻ መውሰድ፣ የጨጓራ ፀረ-አሲድ መድሃኒት፣ የዓይነ ምድር ማለስለሻ እንዲሁም ማሞቂያ ፓዶችን በፍጹም መጠቀም የለብንም አነዚህን የምናደርግ ከሆነ ያበጠው ትርፍ አንጀታችን እንዲፈነዳ እናደርገዋለን፡፡

✔የትርፍ አንጀት ምርመራ

የትርፍ ዘንጀትን ምርመራ በጣም አስቸጋሪ የሚያደርገው ምልክቶች ከሌሎች በሽታዎች ጋር በጣም ተመሳሳይ ስለሆኑ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል፦ የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን፣ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣ ጨጓራ፣ የአንጀት ኢንፌክሽን እና የኦቫሪ ችግር ናቸው፡፡
የሚከተሉት ምርመራዎች በሽታዉን ለማከም የሚደረጉ ናቸው፦
• የከርስ/ሆድ ምርመራ እብጠትን ለማወቅ
• የሽንት ምርመራ፦ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን ለማወቅ
• የፊንጢጣ ምርመራ
• የደም ምርመራ
• ሲቲ ስካን እና/ወይም አልትራሳውንድ

✔ የትርፍ አንጀት በሽታ እንዴት ይታከማል?

በህክምና ቋንቋ አፒንዴክቶሚ የሚባለው ትርፍ አንጀትን ለማስወገድ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ሲሆን መደበኛው(ስታንዳርድ) የትርፍ አንጀት ህክምና ነው፡፡
በአጠቃላይ የትርፍ አንጀት የሚጠረጠር ከሆነ የህክምና ባለሙያው ጥንቃቄን በማስቀደም ከዚያም ትርፍ አንጀት ከመቀደዱ/ከመፈንደቱ በፊት በቀዶ ጥገና በፍጥነት ይወገዳል፡፡
ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚከተሉት የሚፈጠሩ ከሆነ ወዲያው ለሃኪምዎ ያሳውቁ፦
• ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ማስመለስ/ማስታወክ ካለ
• በሆድ ውስጥ ያለው ህመም ከጨመረ
• ድካም ካለ ወይም ፌንት ከሰሩ
• በሚያስመልስዎ ወይም በሽንት ውስጥ ደም ካለ
• የተቀደዱት ቦታ የሚቀላ እና የህመም ስሜት የሚጨምር ከሆነ
• ትኩሳት
• በቁስሉ ላይ መግል የሚታይ ከሆነ

✔የትርፍ አንጀት በሽታን መከላከል ይቻላል?
የትርፍ አንጀት በሽታን በምንም ዓይነት መንገድ መከላከል አንችልም፡፡ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን የሚመገቡ ሰዎች በትርፍ አንጀት በሽታ የመያዝ እድላቸው ዝቅ ያለ ነው፡፡ አሳ፣ ፍራፍሬና አትክልቶች በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች ናቸው፡፡

መልካም ጤንነት!!

biniesh
I am and Ethiopian Blogger and computer Enthusiast.
http://www.binishare.com/wp

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *