ጤናማ ሆነው ለመቆየት እነዚህን 10 ወርቃማ ህጎች ይከተሉ!!
፩. ጤናማ አመጋገብ ይመገቡ
የሚመገቡት ምግብ ለሰውነታችን እንደ ነዳጅ በመሆን ያገለግላሉ። የተመገቡት የምግብ ዓይነት እና መጠን በቀጥታ የጤናዎን ሁኔታ ያስተጓጉላል። ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች በሚመገቡበት ወቅት ሰውነትዎ ለበሽታ በጣም የተጋለጠ ይሆናል።
፪. ድርቀትን ያስወግዱ
ስለ አጠቃላይ የጤናችን ሁኔታ ስንመለከት ሰውነታችን የተትረፈረፈ ፈሳሽ ሊኖረው ግድ መሆኑን እናወራለን። በቂ የሆነ ፈሳሽ ሰውነታችን እንዲኖረው ቀኑን ሙሉ በቂ የሆነ ውሃ መጠጣት አለብን።
፫. አካላዊ እንቅስቃሴን የህይወትዎ አካል ያድርጉ
ጤናማና ከበሽታ ነፃ የሆነ ህይወት ለመምራት መደበኛ የሆነ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ብቸኛው የተሻለ አማራጭ ነው። እንደ ዕድሜዎ ወይም እንደ ብቃትዎ ሁኔታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው።
፬. በተመስጦ ወደውስጥ መተንፈስን ይለማመድ
ጥልቅ ትንፈሳ ወይም በሌላ አገላለጽ የሚቆጣጠሩት አተነፋፈስ ጤናማ እንዲሆኑ በጣም ጠቃሚ የሆነ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በተጨማሪም ጠንካራ የሆነ የሰውነት እና የአእምሮ ግንኙነት እንዲፈጠር ይረዳናል።
፭. የሰውነት ክብደትዎን በንቃት ይከታተሉ
ወደ ሚዛን ላይ መውጣት ልምድዎ በማድረግ የሰውነት ክብደትዎን ቼክ ያድርጉ ወይም ይቆጣጠሩ። የተመጣጠነ የሰውነት ክብደት እንዲኖርዎ በማድረግ ውፍረትን ተከትለው የሚመጡ በሽታዎች እንደ አርትራይተስ፣ የደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመምን በቀላሉ መከላከል ይችላሉ።
፮. ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ
ሲጋራ በጤናዎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው። ሲዲሲ (CDC) ገለፃ ከሆነ በሲጋራ ውስጥ ከ 5,000 በላይ ኬሚካሎች ይገኛሉ እነዚህ ኬሚካሎች ለሰው ጤንነት በጣም ጎጂ ናቸው።
፯. በዘመናዊነት ይዝናኑ
የአልኮል መጠጥ ስንወስድ እንደ ቶኒክ ወይም እንደ መርዝ ይሰራሉ ነገር ግን ይህ የሚወሰነው በቀን ውስጥ የጠጡት መጠን ላይ ነው። መጠነኛ አልኮል መጠጣት ለልብና ለዝውውር ስርዓታችን በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ይወሰዳል። በተጨማሪም በዓይነት ሁለት የስኳር በሽታ እና የሀሞት ጠጠር የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል።
፰. መልካም አመለካከት ይኑርዎት
ለህይወት ጤናማና በጎ አመለካከት መኖር ሌላኛው ጤናማ ህይወት እንድንመራ የሚረዳ ሚስጥር ነው። አነጋገርዎና ለህይወት ያለዎት አመለካከት አጠቃላይ ጤንነትዎ ላይ ቀጥተኛ የሆነ ሚና አለው።
፱. በበዓላትና በዕረፍት ቀኖች ዘና ይበሉ
እያንዳንድ ሰው በማንኛውም ዕድሜ፣ ፆታና የሃብት መጠን ላይ ቢገኙም መዝናናት ያስፈልጋቸዋል። ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ሲፋቱ እረፍትና መዝናናትን ይዞልዎት ይመጣል።
፲. የቤተሰብዎን የጤና ሁኔታ ታሪክ ይወቁ
የቤተሰብዎን የጤና ታሪክ ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው። ስለራስዎና የቅርብ ቤተሰብዎ የተመዘገበ የጤና መረጃ መያዝ በየትኛው የበሽታ ዓይነት የመያዝ ዕድልዎ ከፍተኛ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጥዎታል።
መልካም ጤንነት!!!