ጉበት በላይኛው ቀኝ የሆድ ክፍል የሚገኝ ትልቅ የሰውነት አካል ሲሆን ከአንድ እስከ አንድ ነጥብ አምስት (1-1.5 kg) ኪ.ግ ክብደት ይመዝናል።

የጉበት በሽታ ዋና ዋና መንስዔዎች

ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ

ከልክ ያለፈ ባህላዊ / ዘመናዊ መድኃኒት መጠቀም

በተለያዩ ኬሚካልና ሌላ ነገር የተመረዙ ምግቦች

ልዩ ልዩ የጉበት እጢዎች መፈጠር

በጉበት ቫይረስ መጠቃት ናቸው።

የጉበት በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች

የዓይን ቢጫ መሆን

የሽንት መጥቆር

የሰገራ መንጣት

የሰውነት ማሳከክ

አቅም ማነስ/ድካም

የምግብ ፍላጎት መቀነስ

ማቅለሽለሽና ማስታዎክ

የሆድ ህመምና የሆድ መነፋት ናቸው።

የጉበት ቫይረስ (Hepatitis Virus)

ሄፓ ኤ፣ ሄፓ ቢ፣ ሄፓሲ፣ ሄፓ ዲ፣ ሄፓ ኢ እና ሄፓ ጂ ይባላሉ።

ነገር ግን ከተዘረዘሩት ውስጥ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ዋነኛ የጉበት በሽታን አምጭ ቫይረሶች ናቸው።

በተለይ ሄፓታይተስ ቢ በአለማችን ትልቁን የጤና ቀውስ እያመጣ ያለ ገዳይ ቫይረስ ሲሆን በዓለም ላይ በሄፓታይተስ ቢ ከተያዙት 350,000,000 ሰዎች ውስጥ 1,000,000 ይሞታሉ።

የቫይረሱ ስርጭት በአሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ከ 0.12-2% ሲሆን ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ግን ከ 10-20% እንደሆነ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያረጋግጣሉ።

ዋና ዋና የሄፓታይተስ ቢ እና ሲ መተላለፊያ መንገዶች
መተላለፊያ መንገዶቹ ከ ኤች.አይ.ቪ (HIV) መተላለፊያ ጋር ተመሳሳይ ቢሆኑም የመዛመት አቅሙ ግን ከኤች.አይ.ቪ (HIV) በአስር እጥፍ ይበልጣል።

በልቅ የሆነ ወሲብ

በእርግዝና እን በወሊድ ወቅት ከእናት ወደ ልጅ

በተበከለ መርፌና ምላጭ

በደም ንክኪ ና ከህሙማኑ በሚዎጣ የውስጣዊ ፈሳሽ ንክኪ ናቸው።

የበሽታው ጉዞ አዝጋሚ ወይም አጣዳፊ ሊሆን ይችላል።

በሽታው ምልክት ሳያሳይ በውስጥ ተደብቆ ሊቆይም ይችላል።

ለጉበት ካንሰርም ያጋልጣል።

የጉበት በሽታ ህክምና
ህክምናው በሀገራችን ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማዳን ባይቻልም እንዳማራጭ የምንጠቀማቸው ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ግን እነሆ፦

ኢንተርፌሮን (Enterferone Alfa)

ላሚቩዲን (Lamivudine)

ሪባቪሪን (Rebavirine) ናቸው።

ጠቃሚ ምክር እነሆ፦
ይሄም ቀድሞ መከላከል ሲሆን እንዴት ካሉ ደግሞ እንደሚከተለው ይረዱት…
1ኛ. የ”መ” ህጎችን ማክበር
2ኛ. የሄፓታይተስ ቢ ክትባትን መውሰድ
3ኛ. የጋራ መጠቀሚያ ሹልና ስለታማ ነገሮችን ፈጽሞ ማስወገድ ናቸው።
Post Views: 741