የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች 8 ምርጥ ምግቦች
(በዳንኤል አማረ @ኢትዮጤና) #EthioTena #Diabetics
፩) ገብስ
ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ሰባ በመቶ (70%) ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።
፪) ባቄላ እና ተመሳሳይ ዘሮቹ
ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ
በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና ረሃብ እንዳይኖር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
፫) እንቁላል (በመጠኑ)
እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ
እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት የኮለስትሮል መጠን ከፍ እንዲል አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።
፬) አሳ
የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል አርባ በመቶ (40%) ይቀንሳል።
፭) የአበሻ አይብ
የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።
፮) የወይራ ዘይት
በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ ዘይት ከፍተኛ ፀረ-ኢንፍላማቶሪ (anti inflammatory) ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የመዋጋት ባህሪይ አለው ማለት ነው።
፯) ስኳር ድንች
ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም
ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው።
ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን insulin resistance ይዋጋሉ።
፰) ቀይ ስጋ በመጠኑ
ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ
ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።
መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ይወዳጁ