EDUCATIONAL

የቀይስር 10 የጤና ጥቅሞች

የቀይስር 10 የጤና ጥቅሞች

1. የናይትሬት(Nitrates) ይዘቱ ከፍተኛ ሲሆን ረዘም ላለ ጊዜ የሃይል ምንጭነት ይውላል፡፡ የልብ ጤንነትን ለማሻሻል እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በሚገባ ለመወጣት ይጠቅማል፡፡

2. በብረት(Iron) ንጥረ ነገር የተሞላ ሲሆን በደም ውስጥ ኦክስጂን በትክክል እንዲዘዋወር ይረዳል በተጨማሪም የደም ማነስ በሽታን ይከላከላል፡፡
3. ቤታሌይን(Betalain) የተባለ ፀረ-ኦክሲዳንት የያዘ ሲሆን ሴሎቻችንን ከጉዳት ይጠብቃል እንዲሁም ካንሰርን ይከላከላል፡፡

4. ቫይታሚን ኤ (Vitamin A) በውስጡ የያዘ ሲሆን ለጤናማ የአይን እይታ አስፈላጊ ነው፣ የዳፍንት በሽታን ይከላከላል በተጨማሪም ጤናማ የቆዳ ሴሎች እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

5. ከፍተኛ የፋይበር(Fiber) ይዘት ስላለው ለጤናማ የምግብ ስልቀጣ/መፈጨት ጠቃሚ ነው፡፡ የሆድ ድርቀትን እና ተቅማጥን ይከላከላል እንዲሁም በአንጀት በሽታ የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል፡፡

6. ከተክሎች ለሚገኝ ፕሮቲን ጥሩ ምንጭ ሲሆን ለዘይታማ የሰውነት አካሎቻችን ዕድገት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

7. የፖታሲየም(Potassium) ይዘቱ ከፍተኛ ሲሆን የነርቭ ግብረ መልስ በትክክል እንዲተላለፍ ይረዳል፣ ፈጣን አስተሳሰብ እንዲኖረን ይረዳል በተጨማሪም ግልጽ አስተሳሰብ እንዲኖረን ይረዳል፡፡

8. በፎሊክ አሲድ (Folic Acid) የተሞላ ሲሆን ለጽንስ እድገትና ጥንካሬ አስፈላጊ ነው፡፡

9. በካልሲየም(Calcium) የበለፀገ ሲሆን ለአጥንት ዕድገትና ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ የሆነ ሜኔራል ነው፡፡

10. በቫይታሚን ሲ (Vitamin C) የበለፀገ ሲሆን ቁስል ቶሎ እንዲያገግም ይረዳል፣ ከኢንፌክሽን ይከላከላል በተጨማሪም ጠንካራ በሽታ የመከላከል አቅም እንዲኖረን ይረዳል፡፡

biniesh
I am and Ethiopian Blogger and computer Enthusiast.
http://www.binishare.com/wp

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

10 + = 20