በከንሚንግ ዓለም አቀፍ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አሸነፉ

በከንሚንግ ዓለም አቀፍ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አሸነፉ
***********************************************
ዛሬ በቻይና በተካሄደው የከንሚንግ ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶቹ ምድብ አትሌት በላይ ኦልቀባ በ2፡20፡49 ቀዳሚ ሆኖ በመግባት የቦታውን ክብረ ወሰን ጭምር አሻሽሏል፡፡
በሴቶቹ ደግሞ ፀሃይ ገብሬ ርቀቱን በ2፡35፡00 በመሮጥ አሸናፊ ሆናለች፡፡
ከመላው ዓለም የተውጣጡ ከ20 ሺህ በላይ አትሌቶች በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡
ምንጭ፡- ሺንዋ

Leave A Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *