የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም…
*********************************
የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም የሚረዱ ዘዴዎች
1. ማር
አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አራት ማንኪያ ማር፣ ሩብ ማንኪያ ጨው እና የሎሚ ጭማቂ ጨምረን በማዋሃድ በቀን ከ2 እስከ 3 ጊዜ መጠጣት ጥሩ ወጤት ያስገኛል።
2. በርበሬ እና እርድ
አንድ ብርጭቆ የፈላ ወተት ላይ የእርድ ብናኝ እና ጥቂት በርበሬ ጨምሮ በማዋሃድ ከመኝታ በፊት መጠጣት ህመሙን ያስታግሳል።
3. ካሮት፣ ቀይ ስር እና ኩከምበር
300 ግራም ካሮት፣ 100 ግራም ቀይ ስር እና 100 ግራም ኩከምበር በአንድ ላይ በመፍጨት ጭማቂ በማዘጋጀት መጠቀምም ሌላኛው ለህመሙ መፍትሄ ነው ተብሎ የተጠቀሰ ነው።
4. ሎሚ
አንድ ሎሚ ለሁለት በመክፈል ጨው መነስነስ፤ ከዚያም በመጭመቅ መጠጣትም ጥሩ መፍትሄ ያስገኛል ተብሏል።
5. በረዶ
ብዙዎቻችን በረዶ እንዴት የቶንሲል ህመምን ለመቅረፍ ይረዳል የሚለው ጉዳይ ሊያስገርመን ይችላል።
ነገር ግን በረዶ ችግሩን በማስወገድ ረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው የሚነገረው።
የተወሰኑ የበረዶ ጡቦችን በጨርቅ ጠቅልሎ ወደ ቶንሲል እጢዎች በመላክ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ መቆየት፤ ይህንኑ በቀን ለአራት ጊዜ ማከናወን ህመሙን በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ይረዳል።
6. ዝንጅብል
ዝንጅብል ጨምቀን ሞቅ ካለ ውሃ ጋር ማዋሃድ (ካስፈለገም አንድ ማንኪያ ማር መጨመር ይቻላል)፤ ከዚያም በቀን ለአንድ ወይም ሁለት ጊዜ መጉመጥመጥ።
ዝንጅብልን ሻይ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው።
7. ቀይ ሽንኩርት
ቀይ ሽንኩርት በመፍጨትና ከሞቀ ውሃ ጋር በማዋሃድ አፍን መጉመጥመጥ ህመሙን ለማስታገስ እንደሚያግዝም ተነግሯል።
በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱትን ዘዴዎች በመጠቀም ህመሙ ሊታገስልን ካልቻለ ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው።