NEWS

የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራች ወይዘሮ ዘሚ የኑስ አረፉ

የኒያ ፋውንዴሽና የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራችና ዳይሬክተር ወይዘሮ ዘሚ የኑስ በኮሮናቫይረስ ህመም መሞታቸውን ቢቢሲ ከቅርብ ጓደኛቸው ወይዘሮ እሌኒ ዳምጠው መረዳት ችሏል። ለሳምንታት ያህል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ግንቦት 3፣ 2013 ዓ.ም በጳውሎስ ሆስፒታል ማረፋቸውን የ25 አመት ጓደኛቸው ወይዘሮ እሌኒ ተናግረዋል። ወይዘሮ ዘሚ የኑስ ረመዳን ፆም በገባበት፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 ዓ.ም ሳምንት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲያደርጉ […]