የሰዎችን አእምሮ ማንበብ ይቻላል?
=====================
“ምን አይነት የተለየ ችሎታ ቢኖራችሁ ትመርጣላችሁ?” ተብለው ከተጠየቁ የጥናት ተሳታፊዎች ብዙዎች የሰዎችን አእምሮ ማንበብን ነበር የመረጡት። ይበልጥ አስገራሚው መልስ የመጣው ደግሞ “ችሎታው ቢኖራችሁ የማንን አእምሮ ታነባላችሁ?” ተብሎ ሲጠየቅ ነው። ብዙዎቹ ማንበብ የሚፈልጉት የስነ ጥበብ ሰዎች፣ ሀገር መሪዎች እና የፈላስፎችን አእምሮ ሳይሆን የትዳር አጋራቸውን፣ የአለቃቸውን የጓደኛቸውን…ወዘተ ነበር።
አስበንም ይሁን ሳናስብ፤ ትክክል እንሁንም ስህተት ሁላችንም የሰዎችን አእምሮ እናነባለን። ከሰዎች ጋር ተስማምቶ ለመኖርና ሴኬታማ ህይወት ለመምራት ጓደኛ፣ የስራ ባልደረባ፣ የትዳር አጋርና ቤተሰብን መረዳት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ባላጋራ፣ ተቀናቃኝና ተፎካካሪ የሚያስበውን ማወቅም ጥቅም አለው።
ሀሳብ አይዳሰስም፤ አመለካከት አይታይም፤ እምነት አይለካም፤ ስሜትም እንደዚሁ። ስለዚህ የሰዎችን አእምሮ ማንበብ አስፈላጊ ይሁን እንጂ በግምት ላይ የተመሰረተ ስህተት የመሆን እድል ያለው ፅንሰ ሀሳብ ነው። የሰዎችን ሀሳብ መረዳት ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል። በተቃራኒው ደግሞ የተሳሳተ ግምት ወደ አለመግባባት እና ግፅት ሊመራ ይችላል። “ከመሰለኝ ትክክል ነኝ!” የሚለው ድምዳሜ ላይ ከመድረስ በፊት የራስንም ሀሳብ መመርመር ጥሩ ነው። በተለይ የሰዎችን ሀሳብ ሳናውቅ ስንቀር ምንድነው የምንገምተው?
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው