ነሃሴ 20/2012 – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኃላ በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ተጎድተዋል ወደ ተባሉ አካባቢዎች ተሰማርታ ምልከታ ካካሄደች በኋላ ዛሬ መግለጫ ሰጥታለች ፦
የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት(ከመግለጫው የተወሰደ)፦
“ከሰኔ 22 ቀን ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት በተፈፀመ ጥቃት ከስልሳ ሰባት በላይ ምዕመናን በግፍ እና በአሰቀቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ 38 ምእመናን ቋሚ (ከባድ) 29 ምእመናን ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከሰባት ሺህ በላይ ምእመናን ከመኖሪያቸው ከመፈናቀላቸው ባሻገር በተለያየ ደረጃ ለሚገለፅ ስነ ልቡናዊ እና ስነ አእምሯዊ ቀውስ ተዳርገዋል፣ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረታቸውን በዘረፋ እና በቃጠሎ አጥተዋል”