korona
HEALTH

ስለ ኮሮና ቫይረስ

ኮሮና ቫይረስ ምንድነው?

• የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው።

የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶች

• በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ።

የበሽታው ምልክቶች

• በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል።
• በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋላል።

ምልክቱ የታየባቸው ምን ማድረግ አለባቸው?

• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።
• የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ።
• በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ።
• አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።

ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች፡-

• የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣
• እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣
• ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ
• በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳትን ጋር ንክኪ አለማድረግ

biniesh
I am and Ethiopian Blogger and computer Enthusiast.
http://www.binishare.com/wp

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

+ 81 = 89