Microcephaly

አደገኛው የዚካ ቫይረስ በሽታ

 

አደገኛው የዚካ_ቫይረስ_በሽታ
ዚካ ቫይረስ የፍላቪቫይረስ ዝርያ ሲሆን ከደንጉ ቢጫ ወባና ከምዕራብ ናይል ቫይረስ በሽታዎች ጋር የሚመሳሰል ባህሪ አለው።
ይህ ቫይረስ ዚካ ፌቨር ወይም የዚካ በሽታ ለተባለ በወባ ትንኝ ለሚተላለፍ በሽታ መነሻ ነው ።
የዚካ ቫይረስ በአሁኑ ጊዜ የአለምን ትኩረት እየሳበ የመጣ በሽታ ሊሆን ችሏል ።
የዚህም ምክንያት ጥናት አድታጊዎች በሸታው አዲስ ከተወለደ ህፃን የጤና ችግርና ከአእምሮ ችግሮች ጋር የተያያዘ ሆነው ስላገኙት ነው።
የዚካ ቫይረስ ስርጭት
የዚካ ቫይረስ መጀመሪያ የተገኝው በ1947 ዓ,ም በኢንቴቤ ኡጋንዳ ውስጥ በሚገኝ በዚካ ጫካ ረኽሰስ በሚባል የዝንጀሮ ዝርያ ደም ውስጥ ነው።
ይህ ቫይረስ በሰውና በወባ ትንኝ ውስጥ በኡጋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ናይጀሪያ ፣ አይቮሪ ኮስት ፣ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሉክ እና ማሌዢያ ተገኝቷል።
በ2007 በጣም ከፍተኛ የሆነ የዚካ ቫይረስ ኢንፌክሽን ያፕ በተባለ ደሴት የተከሰተ ሲሆን 75% የመሆነው የህብረተሰብ ክፍል በወረርሽኙ ተጠቅቶ ነበር።
የዚካ ቫይረስ እስከ ሜይ 2015 ድረስ በምዕራብ ንፍቀ ክበብ ስርጭቱ አልተከሰተም ነበር የብራዚል ህብረተሰብ ጤና ባለስልጣን ወረርሽኙ በሰሜን ምስራቅ ብራዚል መከሰቱን እስካረጋገጠበት ድረስ።
በአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት በብራዚል የመጀመሪያው የበሽታው ስርጭት የታዪ ሲሆን ዚካ ቫይረስ በ21 ሀገሮች እና በአሜሪካ ግዛቶች ተሰራጭቷል ።
የዚካ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች
የዚካ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በወባ ትንኝ ንክሻ ይተላለፋል ።
የቫይረሱ ኤደስ በምትባል የወባ ትንኝ ዝርያ ውስጥ ይገኛል ።
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዚካ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው
1. ከሰው ወደ ሰው በደም ልገሳ
2. ከእናት ወደ ልጅ
3. በግብረ ስጋ ግንኙነት
ይተላለፋል ነገር ግን ይህ መተላለፊያ መንገድ የመከሰት ዕድሉ በጣም ጥቂት ነው በአንድ አጋጣሚ ቫይረሱ በወንድ ዘር ፈሳሽ ውስጥ ተገኝቷል ።
ቫይረሱ ተይዘን ምልከት እስከምናሳይበት ያለው ቆይታ በውል የማይታወቅ ባይሆንም ከ 3 – 12 ቀናት እንደሆነ ይገመታል ።

 

የበሽታው ምልክቶች
ከ 20 – 25% በዚካ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ብቻ የበሽታውን ምልከት ያሳያሉ።
በብዙ በሽተኞች ላይ የሚታይ የዚካ በሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።
1. ትኩሳት
2. ሸፍታ
3. የመገጣጠሚያ ህመም
4. የአይን መቅላት
5. የጡንቻ ህመም ናቸው
የዚካ ኢንፌክሽንን የከፋ የሚያደርገው ሁለት ከአእምሮ ጋር የሚያያይዙት ጉዳዮች ስላሉ ነው።
1 በህክምና ቋንቋ ማይክሮሴፋሊ ይባላል ትረጉም የሆነ ችግር ኖሮበት የሚወለድ ህፃን ለማለት ሲሆን የሚወለደው ህፃን ጭንቅላት እጅግ በጣም ያነሰ እና አእምሮ ዕድገቱን ሳይጨርስ ይወለዳል ።
ይህ ችግር የሚያጋጥመው የህፃኑ እናት በመጀመሪያው ትራይሚኒስቴር ወቅት በዚካ የተያዘች እንደሆነ ነው።
2 ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ጉሊያን ባሪ ሴንድሪም ይባላል ይህ ችግር አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ሲሆን የራሳችን የበሽታ መከላከያ ሰርዓት የራሳችን ነርቭ ሴሎች በማጥፋት / በመግደል የጡንቻ መልፈስፈስ ሲያስከትል አልፎ አልፎ ደግሞ ልምሻ ወይም ፓራሊሲስ ያስከትላል ።
የዚካ በሽታ ምርመራ
ለዚካ ኢንፌክሽን የሚያገለግል በብዛት በአለማችን ላይ የምንጠቀምበት ምርመራ የለም አብዛኛው ሰዎች ላይ ምርመራው መሰረት ያደረገው ምልክቶችን በማየትና የሰርጭት ቦታውን በማወቅ ነው።
በላቦራቶሪ ውስጥ ከሚደረጉ ምርመራዎች መካከል ፒ, ሲ, አር ፣ ሴሮሎጂካል ምርመራዎች ኒኩሊክ አሲድ አምፕሊፊኬሽን ምርመራዎች ይጠቅሳሉ ።
የዚካ ቫይረስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገድ
1. የወባ ትንኝን መቆጣጠርና ማጥፋት
በግቢ ውስጥና በአካባቢያችን የተከማቸ ውሃ ዌም ኩሬ ካለ ማስወገድ ።
2. በወባ ትንኝ እንዳንነከስ ራሳችንን መከላከል የበሽታው ሰርጭት ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ ከሆነ በወባ እንዳይነከሱ የግል ጥንቃቄን ማድረግ በሽታው ወደተከሰተበት ቦታዎች አለመሄድ
3. ስለ ዚካ ቫይረስና ወባ ለማህበረሰቡ ማሳወቅ ህብረተሰቡ ስለ ዚካ ቫይረስ እና መከላከያ መንገዶች ማሳወቅ እራሳቸውን ከበሽታው እንዲከላከሉ ማድረግ ።
ጤና ይስጥልኝ። አንብበው ሲጨርሱ like,comment,share በማድረግ መረጃውን ለወዳጅ ዘመድ ያካፍሉ።

ምንጭ ጤናዎ በቤትዎ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *