ቫይረስ ምንድን ነዉ? ቫይረስ እንዴት መከላከል እንችላለን? ⏩በአሁኑ ጊዜ አለማችንን…

ቫይረስ ምንድን ነዉ? ቫይረስ እንዴት መከላከል እንችላለን?
⏩በአሁኑ ጊዜ አለማችንን በየአመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ኪሳራ ላይ እየጣለ የሚገኘዉ ኮምፒዩተር ቫይረስ ምንድን ነዉ? ኮምፒዩተር ቫይረስ የሌሎች ሰዎችን የግል መረጃ ለመስረቅ ወይም ለመለወጥ ፣ የኢ ሜይል አካዉንታቸዉን እንደባለቤት ለመጠቀም ፣ በኮምፒዉተራቸዉ ላይ ያስቀመጡትን መረጃ ለማጥፋት ፣ ኮምፒዉተራቸዉን ከጥቅም ዉጭ ለማድረግ ወይም ለሌላ የተለየ አላማ የተሰሩ ፕሮግራሞች ሲሆኑ በሌሎበማራባት (ሀከሮች) ባለቤቱ ሳያዉቅ ይጫናሉ፡፡ አንድ ጊዜ ወደ ኮምፒዩተራችን ከገቡ በኋላ ራሳቸዉን ልክ ስድስተኛ ክፍል ባዮሎጂ ላይ እንደተማርናቸዉ እዉነተኛ ቫይረሶች በኮምፒዩተራችን ሀርድ ዲስክ ቡት ሴክተር ራም እና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ ራሳቸዉን በሚገርም ፍጥነት በማራባት ኮምፒዩተራችንን ለመረጃ ስርቆትና ቀርፋፋነት ይዳርጉታል፡፡
ቫይረስ ምንድን ነዉ

ቫይረስ ምንድን ነዉ

🔃የኮምፒዩተር ቫይረስ አይነቶች:
(1.)⤵Spyware (ሰላዮች)
እነዚህ ፕሮግራሞች ፕሮግራም የተደረጉት የተጠቂዉን ግለሰብ ወይም ተቋም መረጃ ያለባለቤቱ ፈቃድ ለመስረቅ ሲሆን አንዴ የሚፈልገዉን መረጃ ካገኘ በኋላ መረጃዉን በኢ-ሜይል ወይም ሌሎች መንገዶች ለፕሮግራመሩ (ሀከሩ) ይልካል፡፡ ግለሰቡ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ካልሆነ ወደ ፍላሽ ዲስኮች መረጃዉን በማሸሽ የኢንተርኔት አገልግሎት እስኪያገኝ ድረስ ከኮምፒዩተርኮምፒዩተራችን ኮምፒዩተር ይሽከረከራል፡፡
(2.)⤵Trojan horses (የትሮይ ፈረሶች)
እነዚህ ፕሮግራሞች ልክ እንደ ግሪኩ የትሮይ ፈረስ ራሳቸዉን ጠቃሚ ሶፍትዌር ጌም ቪዲዮ በማስመሰል ዳዉንሎድ እንድናደርጋቸዉ ካደረጉ በኋላ ኢንስታል ስናደርጋቸዉ ያሰብነዉን ሳይሆን ፕሮግራመራቸዉ ያዘዛቸዉን ጥፋት የሚተገብሩ ፕሮግራሞች ናቸዉ፡፡ Trojans ከሌሎች ቫይረሶች የሚለዩት ራሳቸዉን እንዲያባዙ ሆነዉ አለመሰራታቸዉ ነዉ፡፡
(3.)⤵ Ransomware (አጋቾች)
እነዚህ ቫይረሶች አንዴ ዉስጥ ከገቡ በኋላ የኮምፒዩተሩን ሲስተም በመቆጣጠር ኮምፒዩተሩን ወይም የኮምፒዩተሩን የሆነ አገልግሎት (ለምሳሌ ኢንተርኔት) እንዳንጠቀምበት ከቆለፉ በኋላ ኮምፒዩተሩን በድጋሚ ለመጠቀም ከፈለግን ለፕሮግራመሩ (ሀከሩ) የማስለቀቂያ ክፍያ እንድንፈጽም ያስገድዱናል፡፡ የተጠየቅነዉን ክፍያ መክፈል ካልቻልን ከኮምፒዩተራችን ጋር ተቆራርጠን ቀረን ማለት ነዉ ምክንያቱም ቀድሞ የተጫነ አንቲ ቫይረስ ከሌለ አዲስ ጭነን ቫይረሱን ለማጥፋት እንዳንችል ቫይረሱ ስለሚከለክለን ነዉ፡፡
(4.)⤵ Worms (ዎርምስ)
እነዚህ የቫይረስ አይነቶች የተለመዱና በብዛት የሚገኙ ሲሆኑ መረጃን ከመስረቅ ይልቅ መረጃን መደበቅና ማጥፋት የሚቀናቸዉ ናቸዉ፡፡ ፍላሽ ስንሰካ ሾርትከት የሚሆንብን ከሆነና ያስቀመጥነዉ ዳታ ሳናዉቀዉ የሚጠፋብን ከሆነ ኮምፒዩተራችን በዚህ የቫይረስ አይነት ለመጠቃቱ ምልክት ነዉ፡፡
(5.)⤵ Keyloggers (ኪሎገርስ)
አስገራሚ አሰራር ያላቸዉ የቫይረስ አይነቶች ሲሆኑ ተጠቂዉን ሰዉ ባለመረበሽና ፋይል ባለመንካት ይታወቃሉ፡፡ ታዲያ ፋይል ካልሰረቁ ና ተጠቃሚዉን ካልረበሹ ምንድነዉ ቫይረስ የሚያስብላቸዉ የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፡፡ Keyloggers በዋነኝነት የሚሰሩት ስራ ተጠቂዉ በኮምፒዩተሩ ኪቦርድ ላይ የሚጽፋቸዉን ጽሁፎች ፓስወርዶች እና ሌሎች መረጃዎችን መመዝገብ ሲሆን የግለሰቡን ፓስወርዶች የባንክ መረጃዎች ወዘተ…በቀላሉ ኪቦርዱን ስንጫን የትኛዉን Key እንደተጫንን መዝግበዉ ለፕሮግራመራቸዉ ያስተላልፉልናል፡፡ ከዚያ በኋላ የተሰረቅነዉን መረጃ ተንትኖ ለሚፈልገዉ ተግባር መጠቀም የሀከሩ ተግባር ይሆናል፡፡
የኮምፒዩተር ቫይረስ አይነቶች ብዛት ከላይ ለምሳሌ በተጠቀሱት አይነቶች ብቻ የተወሰኑ አይደሉም፡፡ ነገር ግን ስለ ኮምፒዩተር ቫይረስ አይነቶችና የሚያደርሱት ጥፋት በጨረፍታ ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ ዝርዝር ነዉ፡፡

ጥሩ ከሚባሉት ፀረ-ቫይረስ ፕሮግራሞች አንዱን ከዚህ ዳውንሎድ ያርጉ AVAST ANTIVIRUS DOWNLOAD
instructions if download failed
wait 5 sec for the advertisement to load and click continue 2 times.

ምንጭ፦ ስለ ቴክኖሎጂ እንነጋገር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *